በ 2026 ወላጆችን ወደ ካናዳ ለማምጣት ያለው ብቸኛ አማራጭ? ሱፐር ቪዛ (Super Visa)
- Melaku Abebe
- 6 hours ago
- 2 min read

ብዙዎች ወላጆቻቸውን ወይም አያቶቻቸውን በቋሚነት ለማስመጣት (Parent and Grand Parent Sponsorship) የካናዳ መንግስት የሎተሪ ዕድል እንዲከፍት ሲጠባበቁ ነበር። ሆኖም ግን በ 2026 የካናዳ መንግስት ባወጣው አዲስ መመሪያ መሠረት፣ ለአዲስ አመልካቾች የወላጆች እና አያቶች የቋሚ መኖሪያ ፈቃድ (PR) ስፖንሰርሺፕ ዝግ ሆኖ ይቆያል።
በአሁኑ ወቅት ወላጆችን ለረጅም ጊዜ ቆይታ (ከ6 ወር በላይ) ወደካናዳ ለማምጣት ያለው ብቸኛ እና አስተማማኝ አማራጭ የሱፐር ቪዛ (Super Visa) ነው።
ሱፐር ቪዛ (Super Visa) ምንድን ነው?
ሱፐር ቪዛ ለወላጆች እና ለአያቶች ብቻ የሚሰጥ ልዩ ቪዛ ሲሆን፣ ከተለመደው የጎብኝ ቪዛ (Visitor Visa) የሚለየው ለረጅም ጊዜ በካናዳ እንዲቆዩ ስለሚፈቅድ ነው።
የቆይታ ጊዜ፦ በሱፐር ቪዛ የገቡ ወላጆች በአንድ ጊዜ እስከ 5 ዓመት ድረስ በካናዳ መቆየት ይችላሉ።
የቪዛው ርዝመት፦ ቪዛው እስከ 10 ዓመት ድረስ ሊያገለግል ይችላል።
ለሱፐር ቪዛ የሚያስፈልጉ ዋና ዋና መስፈርቶች (2026)
ወላጆቻችሁን ለመጋበዝ እናንተ (ልጆች ወይም የልጅ ልጆች) የሚከተሉትን ማሟላት ይኖርባችኋል።
1. የገቢ መጠን (Low Income Cut-Off (LICO)
ጋባዡ በቂ ገቢ እንዳለው ማሳየት አለበት። በ 2026 የወጣው ዝቅተኛ የገቢ መጠን (Low Income Cut-Off) እንደ ቤተሰብ ብዛት ይለያያል፦
ለ 2 ሰው ቤተሰብ፦ $38,002
ለ 3 ሰው ቤተሰብ፦ $46,720
ለ 4 ሰው ቤተሰብ፦ $56,724
ለ 5 ሰው ቤተሰብ፦ $64,336 (ማሳሰቢያ፦ የቤተሰብ ብዛት ሲቆጠር ጋባዡን፣ ባለቤቱን፣ ልጆቹን እና የሚመጡትን ወላጆች ይጨምራል)
2. የጤና መድህን (Medical Insurance)
ይህ በጣም አስፈላጊው መስፈርት ነው። ከካናዳ የኢንሹራንስ ኩባንያ ቢያንስ ለ 1 ዓመት የሚቆይ እና ቢያንስ $100,000ሽፋን የሚሰጥ የጤና መድህን መገዛት አለበት።
3. የህክምና ምርመራ (Medical Exam)
ወላጆች ቪዛው ከመሰጠቱ በፊት በካናዳ መንግስት እውቅና በተሰጣቸው ሃኪሞች ዘንድ የጤና ምርመራ ማድረግ ይኖርባቸዋል።
በተጨማሪ
የግብዣ ደብዳቤ (Invitation Letter)፦ በደብዳቤው ላይ ለወላጆቻችሁ በቆይታቸው ወቅት የገንዘብ ድጋፍ እንደምታደርጉላቸው በግልጽ መጥቀስ እና የቤተሰብ ዝርዝር ማካተት አለባችሁ።
የንብረት እና የቤተሰብ ትስስር፦ ወላጆቻችሁ በኢትዮጵያ ያላቸውን ንብረት፣ ቤት፣ ወይም ሌሎች የቤተሰብ ትስስሮች ማሳየታቸው ቪዛ የመሰጠት እድሉን ይጨምረዋል።
ወላጆችዎን በሱፐር ቪዛ አማካኝነት ወደ ካናዳ ማምጣት ያስባሉ? ያግኙን!
ኤምቲኤ የኢሚግሬሽን አገልግሎት

Comments