top of page

ፕሮቪንሺያል ኖሚኒ ፕሮግራም

PNP የካናዳ ግዛቶች በአንድ የተወሰነ ክፍለ ሀገር ወይም ግዛት ውስጥ መኖር የሚፈልጉ እና ለኤኮኖሚ ዕድገቱ አስተዋፅዖ ያደርጋሉ ብለው ያሰቧቸውን እጩ ግለሰቦችን መምረጥ የሚያስችላቸው ፕሮግራም ነው ። የተሳካላቸው እጩዎች በካናዳ ውስጥ ለቋሚ መኖሪያነት ማመልከት ይችላሉ።

!
Widget Didn’t Load
Check your internet and refresh this page.
If that doesn’t work, contact us.

በPNP ለመሳተፍ ብቁ የሆኑት እነማን ናቸው?

እያንዳንዱ የካናዳ ክልል (ለምሳሌ፡ ኦንታሪዮ፣ አልበርታ፣ ማኒቶባ፣ ሳስካችዋን) የራሱ የሆነ መስፈርት አለው። በአብዛኛው የሚከተሉትን ይፈልጋሉ፦

  • የተፈላጊ ሙያ ባለቤት: ክልሉ በወቅቱ በሚፈልገው የስራ መስክ (ለምሳሌ፡ በጤና፣ በቴክኖሎጂ፣ በእርሻ) ልምድ ያለው።

  • ከክልሉ ጋር ቁርኝት ያለው: በዚያ ክልል የሚኖር ዘመድ ያለው ወይም ከዚህ በፊት በዚያ ክልል ተምሮ/ሰርቶ የሚያውቅ።

  • የስራ ቅጥር ጥያቄ (Job Offer): በዚያ ክልል ውስጥ ከሚገኝ ቀጣሪ ድርጅት የስራ ቅጥር ጥያቄ የቀረበለት

 

ማስታወሻ፡ የኩቤክ (Quebec) ግዛት የራሱ የሆነ የተለየ የአመራረጥ ስርዓት ስላለው በዚህ ፕሮግራም ውስጥ አይካተትም።

2

ይህ አማራጭ ለምን ይጠቅማል?

ብዙዎች በኤክስፕረስ ኢንትሪ ብቻ ሲወዳደሩ ነጥባቸው (CRS Score) ዝቅተኛ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን በአንድ ክፍለ-ሀገር ከተመረጡ (Nominated)፡

  • በኤክስፕረስ ኢንትሪ ፕሮፋይልዎ ላይ 600 ተጨማሪ ነጥብ ያገኛሉ።

  • ይህ ማለት በሚቀጥለው የዕጣ አወጣጥ ላይ ወደ ካናዳ እንዲመጡ መጋበዝዎ (Invitation to Apply) የተረጋገጠይሆናል ማለት ነው።

ያግኙን

+1 647-563-6059

  • Facebook
  • LinkedIn

እናመሰግናለን!

bottom of page