top of page

የወላጆች ስፖንሰርሺፕ

!
Widget Didn’t Load
Check your internet and refresh this page.
If that doesn’t work, contact us.

የካናዳ ዜጎች እና ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸው ነዋሪዎች ወላጆቻቸው እና አያቶቻቸው ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ አግኘተው ወደ ካናዳ መጥተው እንዲኖሩ ስፖንሰር ማድረግ ይችላሉ። ይህ ፕሮግራም ከሱፐር ቪዛ የሚለይ ሲሆን ሱፐር ቪዛ ረዘም ያለ የጉብኘት ጊዜን የሚፈቅድ የወላጆች ቪዛ ሲሆን ይህኛው ፕሮግራም ግን ወላጆች ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ አግኝተው በዘላቂነት በካናዳ እንዲኖሩ እድልን የሚያመቻች ነው፨

ይህ ፕሮግራም ወላጆች በቋሚነት ከልጆቻቸው ጋር እንዲኖሩ ኋላም የካናዳ ዜግነትን እንዲያገኙ እድል የሚፈጥር ከመሆኑ አንፃር በብዙዎች በጣም ተፈላጊ እና በዕጣ የሚወጣ ሲሆን እድሉን ለማግኘት ተዘጋጅቶ መጠበቅን የሚጠይቅ ነው፨

ስፖንሰር ለመሆን ምን መስፈርቶችን ማሟላት ይኖርብኛል?

ወላጆችዎን ወይም አያቶችዎን ለቋሚ መኖሪያ ፈቃድ ስፖንሰር ለማድረግ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርብዎታል፦

  • ዕድሜ፦ ቢያንስ 18 ዓመት የሞላዎት መሆን።

  • መኖሪያ፦ በካናዳ ውስጥ የሚኖሩ መሆን።

  • የመኖሪያ ፈቃድ ሁኔታ፦ የካናዳ ዜጋ፣ በቋሚ ነዋሪነት (Permanent Resident) የሚኖሩ ወይም በካናዳ የነገዶች ሕግ (Indian Act) መሠረት የተመዘገቡ ተወላጅ መሆን።

  • የገቢ መጠን፦ አነስተኛውን አስፈላጊ ዓመታዊ ገቢ (Minimum Necessary Income - MNI) ማሟላት።

  • የድጋፍ ቃል ኪዳን፦ ስፖንሰር ለሚያደርጓቸው የቤተሰብ አባላት ለተወሰነ ጊዜ የገንዘብ ድጋፍ ለመስጠት የመንግሥት ውል (Undertaking) መፈረም መቻል።

ተጨማሪ መረጃ፦ ወላጆችን ወይም አያቶችን ስፖንሰር ለማድረግ በቅድሚያ ለካናዳ የኢሚግሬሽን፣ ስደተኞች እና ዜግነት መሥሪያ ቤት (IRCC) የፍላጎት መግለጫ (Interest to Sponsor) ማስገባት ይኖርብዎታል። በዕጣ ከተመረጡ በኋላ ብቻ ለስፖንሰርሺፕ ለማመልከት ጥሪ/ግብዣ (Invitation to Apply) ይደርስዎታል።

2

ስፖንሰር አድራጊ የሚኖርበት ሃላፊነት?

አንድ ስፖንሰር አድራጊ ወላጆቹ ወደ ካናዳ ከመጡ በኋላ ለ20 ዓመታት የሚቆይ የገንዘብ ድጋፍ ስምምነት (Undertaking) ከመንግሥት ጋር ይፈርማል። በዚህም መሠረት ወላጆቹ የመንግሥትን የገንዘብ ድጎማ ሳይጠይቁ እንዲኖሩ የሚከተሉትን መሠረታዊ ፍላጎቶች የማሟላት ግዴታ ይኖርበታል፦

  • ምግብ፣ ልብስ፣ መጠለያ እና ሌሎች የዕለት ተዕለት ፍላጎቶችን ማቅረብ።

  • በመንግሥት የጤና ሽፋን (OHIP እና መሰል) ያልተካተቱ የጤና ወጪዎችን (ለምሳሌ፦ የጥርስ፣ የዓይን ሕክምና እና መድኃኒቶች) መሸፈን።

ይህ የ20 ዓመት ግዴታ በሚከተሉት ሁኔታዎች ሊሰረዝ ወይም ሊቋረጥ አይችልም፦

  • ወላጆቹ የካናዳ ዜጋ ቢሆኑም፤

  • ከወላጆች ጋር ያለው ግንኙነት ቢሻክር ወይም ቢቋረጥ፤

  • ወላጆች ወደ ሌላ ግዛት ወይም ከተማ ቢዛወሩ፤

  • ስፖንሰር አድራጊው የገንዘብ ችግር ቢገጥመው (ለምሳሌ፦ ሥራ ቢፈታ፣ ገቢው ቢቀንስ ወይም ዕዳ ውስጥ ቢገባ)።

3

የማመልከቻው ሂደት

  1. የፍላጎት መግለጫ (Interest to Sponsor) ማቅረብ፦ በየዓመቱ የIRCC አመልካቾች እንዲመዘገቡ በሚፈቅድበት ወቅት፣ መሠረታዊ መረጃዎችን (ሙሉ ስም፣ አድራሻ፣ የትውልድ ቀን እና ሌሎች አስፈላጊ ዝርዝሮችን) በማካተት የፍላጎት መግለጫዎን በኢንተርኔት ያቅርቡ።

  2. የምዝገባ ማረጋገጫ መቀበል፦ የፍላጎት መግለጫዎ በትክክል መገባቱን የሚያረጋግጥ የቁጥር መለያ (Confirmation Number) ይደርስዎታል። ይህ ቁጥር ማመልከቻዎ በምን ደረጃ ላይ እንዳለ ለመከታተል ስለሚያስፈልግ በጥንቃቄ መያዝ ይኖርብዎታል።

  3. ለማመልከት ግብዣ (Invitation to Apply) ማግኘት፦ በዕጣ (Random Selection) ከተመረጡ፣ ሙሉ የስፖንሰርሺፕ ማመልከቻዎን ለማስገባት የ60 ቀናት የጊዜ ገደብ ይሰጥዎታል። በዚህ ጊዜ ውስጥ ሁሉንም ደጋፊ ሰነዶች እና ክፍያዎችን አሟልተው ማቅረብ ይኖርብዎታል።

4

ስፖንሰር ማድረግ የማይችሉ እነማን ናቸው?

የሚከተሉት ሁኔታዎች ውስጥ የሚገኙ አመልካቾች ወላጆችን ወይም አያቶችን ስፖንሰር ለማድረግ ብቁ ላይሆኑ ይችላሉ፦

  • በእስር ላይ የሚገኙ ከሆነ፤

  • ያልተከፈለ የኪሳራ (Bankruptcy) ዕዳ ካለብዎት፤

  • ከዚህ ቀደም በገቡት የስፖንሰርሺፕ ውል (Undertaking) መሠረት ግዴታዎን መወጣት ተስኖዎት ከሆነ፤

  • በፍርድ ቤት የታዘዘ የትዳር አጋር ወይም የልጅ ቀለብ (Support payments) ሳይከፍሉ ከቀሩ፤

  • ያልተከፈለ የኢሚግሬሽን ብድር ካለብዎት፤

  • በከባድ ወንጀል ተፈርዶብዎት የወንጀል መዝገብዎ ያልተሰረዘ (Pardon/Record Suspension ያላገኙ) ከሆነ።

5

አመራጭ መንገድ፡ ሱፐር ቪዛ

የስፖንሰርሺፕ ማመልከቻዎ በዕጣ ካልተመረጠ እና ፈጣን መፍትሄ የሚፈልጉ ከሆነ፣ ሱፐር ቪዛን እንዲጠቀሙ እንመክራለን። ሱፐር ቪዛ ወላጆችዎ ወይም አያቶችዎ ወደ ካናዳ መጥተው በአንድ ጊዜ እስከ 5 ዓመታት ድረስ እንዲቆዩ ይፈቅዳል።

ይህ ቪዛ በአጠቃላይ እስከ 10 ዓመት የሚያገለግል ሲሆን፣ ደጋግሞ ወደ ካናዳ ለመመላለስ (Multiple Entry) ያስችላል።

ያግኙን

+1 647-563-6059

  • Facebook
  • LinkedIn

እናመሰግናለን!

bottom of page