top of page

ጊዜያዊ የመኖሪያ ፈቃድ

!
Widget Didn’t Load
Check your internet and refresh this page.
If that doesn’t work, contact us.

ጊዜያዊ የመኖሪያ ፍቃድ (TRP)  ወደ ካናዳ ለመግባት መስፈርቱን የማያሟሉ ነገር ግን  አሳማኝ ምክንያት ላላቸው ግለሰቦች በጊዜያዊነት ወደ ሀገር ውስጥ ለመግባት እንዲችሉ የሚሰጥ ልዩ የፍቃድ ወረቀት ነው።

TRP የሚያስፈልገው ማነው?

የጊዜያዊ ነዋሪነት ፈቃድ (TRP)፣ በሕግ ምክንያት ወደ ካናዳ መግባት ለተከለከሉ (Inadmissible) ግለሰቦች በልዩ ሁኔታ የሚሰጥ የመግቢያ ፈቃድ ነው። ይህ ፈቃድ የሚሰጠው አንድ ግለሰብ ወደ ካናዳ እንዲገባ የተፈለገበት አሳማኝ ምክንያት፣ ግለሰቡ ከሚያስከትለው የጤና ወይም የደኅንነት ስጋት ይልቅ ሚዛን ደፍቶ ሲገኝ ብቻ ነው።

ግለሰቦች ወደ ካናዳ እንዳይገቡ ክልከላ ሊጣልባቸው የሚችልባቸው ዋና ዋና ምክንያቶች፦

  • የወንጀል ታሪክ፦ ቀደም ሲል የተፈረደባቸው የወንጀል ክሶች ወይም የሕግ ጥሰቶች ካሉ፤

  • የጤና እክሎች፦ በካናዳ የሕዝብ ጤና ላይ ስጋት ሊፈጥሩ የሚችሉ ወይም በጤና ሥርዓቱ ላይ ከፍተኛ ጫና የሚፈጥሩ የጤና ጉዳዮች ሲኖሩ፤

  • የመረጃ ማጭበርበር (Misrepresentation)፦ በኢሚግሬሽን ማመልከቻ ወቅት የተሳሳተ መረጃ የሰጡ ወይም እውነተኛ ሰነዶችን ደብቀው የተገኙ፤

  • ሌሎች የኢሚግሬሽን ጥሰቶች፦ ቀደም ሲል የቪዛ ጊዜን ማሳለፍ ወይም ያለፈቃድ መሥራትን የመሳሰሉ የኢሚግሬሽን ሕግጋትን የጣሱ።

2

TRP ለምን ያህል ጊዜ ያገለግላ?

የTRP የፈቃድ ርዝማኔ በጉብኝቱ ዓላማ ላይ የተመሰረተ ሲሆን ከጥቂት ቀናት እስከ ሶስት አመታት ሊደርስ ይችላል። እንደየሁኔታውም ሊራዘም ይችላል.

3

TRPን ለማመልከት የሚያስፈልጉ ሰነዶች ምንድን ናቸው?  

በአጠቃላይ ለጊዜያዊ ነዋሪነት ፈቃድ (TRP) ማመልከቻ የሚያስፈልጉ ዋና ዋና ሰነዶች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

  • የማመልከቻ ማብራሪያ ደብዳቤ (Statement of Intent)፦ ወደ ካናዳ ለመግባት የፈለጉበትን አሳማኝ ምክንያት እና የቆይታዎን አስፈላጊነት በዝርዝር የሚያስረዳ ደብዳቤ።

  • የአሳማኝ ምክንያቶች ማስረጃ፦ ለጉዞዎ ምክንያት የሆኑ ጉዳዮችን የሚደግፉ ሰነዶች (ለምሳሌ፦ የሕክምና ማስረጃ፣ የዝምድና ማረጋገጫ፣ የሥራ ቅጥር ደብዳቤ ወይም የንግድ ስብሰባ ጥሪ)።

  • የክልከላ ማስረጃ ሰነዶች፦ ወደ ካናዳ እንዳይገቡ የተከለከሉበትን ምክንያት በዝርዝር የሚገልጹ ሰነዶች (ለምሳሌ፦ የፍርድ ቤት የውሳኔ መዝገቦች፣ የፖሊስ ሪፖርት ወይም ከክልከላው ለመፈወስ የተከናወኑ ተግባራትን የሚያሳዩ እንደ የወንጀል ማገገሚያ/Criminal Rehabilitation ያሉ ሰነዶች)።

  • የመመለሻ ዋስትና፦ በካናዳ የሚኖረዎት ቆይታ ሲያበቃ ወደ ሀገርዎ ለመመለስ ያለዎትን ዝግጁነት የሚያሳዩ ማስረጃዎች።

ማሳሰቢያ፦ የTRP ማመልከቻ ውሳኔ የሚሰጠው በኢሚግሬሽን መኮንኑ የግል እይታ (Discretion) ላይ ተመስርቶ ስለሆነ፣ የሚቀርቡት ማስረጃዎች በጣም ጠንካራ እና አሳማኝ መሆን ይኖርባቸዋል።

bottom of page