top of page

ስለ እኛ

መላኩ በኢትዮጵያ ከሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪውን ያገኘ ሲሆን፣ በካናዳ ከኩዊንስ (Queen’s) ዩኒቨርሲቲ በኢሚግሬሽን እና ዜግነት ሕግ የድህረ-ምረቃ ዲፕሎማ (Graduate Diploma) በከፍተኛ ማዕረግ ተመርቋል። መላኩ በካናዳ የኢሚግሬሽን እና የዜግነት ጉዳዮችን ለማስፈጸም የሕግ ፈቃድ ያለው ባለሙያ ነው።

ኤምቲኤ ኢሚግሬሽን አገልግሎት በጥገኝነት ጥያቄ፣ በስደተኞች ስፖንሰርሺፕ፣ በትዳር አጋር ስፖንሰርሺፕ፣ በቪዛ ማመልከቻዎች እንዲሁም በቋሚ መኖሪያ ፈቃድ እና ዜግነት ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ልምድና እውቀት አለው። ለደንበኞቻችንም ግላዊ፣ ሙያዊ እና አስተማማኝ የኢሚግሬሽን መፍትሄዎችን እናቀርባለን። “ህልማችሁን በጋራ እንቃኝ!” በሚለው መሪ ቃላችን በመመራት፣ የኢሚግሬሽን ጉዞዎ ስኬታማና ከጭንቀት የጸዳ እንዲሆን ልናገለግልዎ ዝግጁ ነን።

ICRC

Melaku T. Abebe

IMG_0611_edited.jpg
bottom of page