የትምህርት ፍቃድ
ከ6 ወር እና ከዛ በላይ ለሆነ ጊዜ በካናዳ ለመማር የሚያስቡ ከሆኑ የትምህርት ፍ ቃድ ያስፈልጎታል፨ የትምህርት ፈቃድ የሚሰጠዎ በካናዳ አለምአቀፍ ተማሪዎችን ተቀብለው ማስተማር በተፈቀደላቸው ኮሌጆች እና ዩኒቨርስቲዎች ብቻ ከተመዘገቡ ነው፨ ለዚህ ተለይተው በተመረጡ ተቋመት ካልተመዘገቡ የትምህርት ፈቃድ አያገኙም፨ መስፈርቱን አሟልተው ሲገኙ የትምሀርት ፈቃድ ደብዳቤ እና ቪዛ አንድ ላይ ይሰጥዎታል፨

1
የትምህርት ፈቃድ እንድታገኙ እንዴት እንደምናግዝዎ
የትምህርት ፈቃድ ሂደት ፈታኝ ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን ቀላል እና ከጭንቀት የጸዳ ለማድረግ ልናገለግልዎ አለን። እንዴት መርዳት እንደምንችል እነሆ፡-
-
ከትምህርት ተቋሙ የምዝገባ ደብዳቤ -
የማመልከቻዎ ወሳኝ የመጀመሪያ ደረጃ ፍቃድ ከተሰጠው የትምህርት ተቋም ተቀባይነት እንዳገኙ የሚያሳየውን የምዝገባ ደብዳቤ እንዲያገኙ እናግዝዎታለን።
2 የገንዘብ አቅም እንዳሎት ማረጋገጫ - የትምህርት ክፍያን፣ የኑሮ ወጪን እና የመመለሻ መጓጓዣን ለመሸፈን በቂ ገንዘብ እንዳሎት እንዴት ማሳየት እንደሚችሉ እንመራዎታለን።
3 የሰነድ ዝግጅት - ከህጋዊ ፓስፖርቶች እስከ ግላዊ የሰነድ ዝርዝሮች፣ ሁሉም አስፈላጊ ሰነዶች ለማስገባት ዝግጁ እንደሆኑ እናረጋግጣለን።
የማመልከቻዎን ትክክለኛነትን እና ተቀባይነትን በማረጋገጥ ማመልከቻዎን በIRCC ፖርታል በኩል በማጠናቀቅ እና በማስረከብ እንረዳለን።
4 የአሻራ እና የሕክምና ምርመራ - ካስፈለገ፣ በባዮሜትሪክ እና በህክምና ምርመራ ሂደት ውስጥ እንመራዎታለን።
5 የጊዜ አጠቃቀም
ማመልከቻዎች ጊዜ ሊወስዱ ይችላሉ. የአካዳሚክ የመጀመሪያ ቀንዎን ለማሟላት በጊዜው ማስገባትን በማረጋገጥ አስቀድመን ለማቀድ እንረዳዎታለን።
2
የፈቃድ ጊዜ እና ሁኔታዎች
የትምርት ፈቃድዎ ሙሉ የትምህርት ፕሮግራምዎ የሚቆይበትን ጊዜ እና ተጨማሪ 90 ቀናት ያጠቃልላል። ተጨማሪ 90 ቀናቶች ከካናዳ ለመውጣት እንዲዘጋጁ ወይም ቆይታዎን ለማራዘም እንዲያመለክቱ የሚያስችልዎ ነው።
የትምህርት ፈቃድዎ ላይ የተቀመጡ ሁኔታዎችን ሁልጊዜም ማክበር አስፈላጊ ነው፣ እነዚህ ሁኔታዎች በስራ ቅጥር ላይ ገደቦችን የሚጥሉ ወይንም ፈቃድ በተሰጠው የትምህርት ተቋም ውስጥ ትምህርትዎን ለማስቀጠል የሚያስፈልጉትን መስፈርቶች የሚያስቀምጡ ናቸወ።
3
እንዴት ማመልከት እንደሚቻል
በካናዳ የትምህርት ፈቃድ ለማግኘት አመልካቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፦
-
የቅበላ ደብዳቤ፦ ዓለም አቀፍ ተማሪዎችን ለመቀበል ፈቃድ ካለው የትምህርት ተቋም (DLI) የተሰጠ የቅበላ ደብዳቤ ማቅረብ።
-
የፋይናንስ አቅም፦ የትምህርት ክፍያን፣ በካናዳ ለኑሮ የሚያስፈልጉ ወጪዎችን እና የመመለሻ የጉዞ ወጪን ለመሸፈን የሚያስችል በቂ ገንዘብ እንዳለዎት ማሳየት (ለምሳሌ፦ የባንክ መግለጫ ወይም የደጋፊ/Sponsor ደብዳቤ)።
-
የደኅንነት ምርመራ፦ የካናዳን ሕግ አክብረው የሚኖሩና የወንጀል መዝገብ የሌለባቸው መሆን (የፖሊስ ማረጋገጫ ሊጠየቅ ይችላል)።
-
የጤና ምርመራ፦ በመልካም የጤና ሁኔታ ላይ መሆን (አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የሕክምና ምርመራ ውጤት ማቅረብ)።
-
ወደ ሀገር የመመለስ ዕቅድ፦ የትምህርት ጊዜውን ሲያጠናቅቁ ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ፍላጎት እንዳላቸው ለኢሚግሬሽን መኮንኑ ማሳመን መቻል።
-
የትምህርት ዓላማ መግለጫ (LOI)፦ የጥናት ፈቃድ ለምን እንደሚያስፈልግ፣ የመረጡት የትምህርት መስክ ለወደፊት የሥራ ሕይወትዎ ያለውን ጠቀሜታ እና ለምን ካናዳን እንደመረጡ የሚያስረዳ አሳማኝ የጥናት ዕቅድ ማቅረብ።
አዲስ መመሪያ (ከኖቬምበር 2024 ጀምሮ )፦ የካናዳ መንግሥት ባወጣው አዲስ መመሪያ መሠረት፣ በትምህርት ተቋም (DLI) መመዝገብ ብቻውን በቂ አይደለም። በተጨማሪም፣ የትምህርት ተቋሙ ከሚገኝበት የግዛት መንግሥት የግዛት ማረጋገጫ ደብዳቤ (Provincial Attestation Letter - PAL) ማግኘት ግዴታ ነው። ይህንን ማረጋገጫ ሳይይዙ የጥናት ፈቃድ ማመልከቻ ቢያስገቡ ማመልከቻው ተቀባይነት አይኖረውም።
4
የትምህርት ፍቃድ ማራዘሚያ፡-
የትምህርት ፈቃድዎ ሊያልቅ ከሆነ እና በካናዳ ትምህርትዎን መቀጠል ከፈለጉ፣ ፍቃድዎን ለማራዘም ማመልከት ይችላሉ። ብቁ ለመሆን የሚከተሉትን ቅድመ ሁኔታዎች ማሟላት አለቦት፡
-
የፈቃድ ጊዜው ከማለቁ በፊት ማመልከቻዎን ያስገቡ።
-
የትምህርት ፈቃድዎን ሁኔታዎች ጠብቀው ትምርትዎን ከተከታተሉ።
-
በካናዳ ውስጥ ለመማር የሚያስችልዎ መስፈርቶችን ጠብቀው ካቆዩ።
የትምህርት ፍቃዴ አገልግሎቱ ካበቃ ምን ይከሰታል?
ተማሪዎች የትምህርት ፍቃዳቸው አገልግሎቱ ቢያበቃም እንኳን የሚከተሉትን መስፈርቶች እስካሟሉ ድረስ ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ ተፈቅዶላቸዋል፡-
-
የትምህርት ፍቃድ እድሳት ማመልከቻቸውን የመጀመሪያው ፍቃድ ጊዜ ከማብቃቱ በፊት ካስገቡ
-
የማራዘሚያ ማመልከቻቸውን ካናዳ ውስጥ ሆነው እየጠበቁ ከሆነ።
-
የትምህርት ፈቃድዎን ሁኔታዎች ማክበርዎን ከቀጠሉ።



