ዜግነት

የካናዳ ዜግነት ለማመልከት መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች
የካናዳ ዜግነት ለማግኘት ማመልከቻ ከማስገባትዎ በፊት፣ የሚከተሉትን ዋና ዋና መስፈርቶች ማሟላትዎን ያረጋግጡ፦
-
የቋሚ ነዋሪነት ፈቃድ (Permanent Resident Status): ህጋዊ የሆነ የካናዳ ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ (PR) ሊኖርዎት ይገባል።
-
በካናዳ የኖሩበት ጊዜ (Physical Presence): ማመልከቻዎን ከማስገባትዎ በፊት ባሉት 5 ዓመታት ውስጥ፣ ቢያንስ ለ3 ዓመታት (ለ1,095 ቀናት) በካናዳ ውስጥ በአካል መኖር አለብዎት። በእስር ቤት ወይም በሙከራ ጊዜ (Probation/Parole) ያሳለፉት ጊዜ አይቆጠርም።
-
የግብር (ታክስ) ሪፖርት (Income Tax Filing): ማመልከቻ ከማስገባትዎ በፊት ባሉት 5 ዓመታት ውስጥ፣ ቢያንስ ለ3 ዓመታት ዓመታዊ የግብር (Income Tax) ሪፖርት ማቅረብ ይጠበቅብዎታል።
-
የቋንቋ ችሎታ (Language Requirement): እድሜዎ ከ18 እስከ 54 ዓመት ከሆነ፣ የእንግሊዝኛ ወይም የፈረንሳይኛ ቋንቋ የመግባባት ችሎታ እንዳለዎት ማረጋገጫ ማቅረብ አለብዎት። የቋንቋ ፈተና ውጤትዎ (CLB) ቢያንስ Level 4 እና ከዚያ በላይ መሆን አለበት።
-
የዜግነት ፈተና (Citizenship Test): እድሜዎ ከ18 እስከ 54 ዓመት ከሆነ፣ ስለ ካናዳ ታሪክ፣ መብቶች፣ ግዴታዎች እና የመንግስት አወቃቀር የሚመዝነውን የዜግነት ፈተና መውሰድ እና ማለፍ ይጠበቅብዎታል።
-
ከወንጀል ነጻ መሆን (Prohibitions): በካናዳ ውስጥ ወይም ከካናዳ ውጪ ወንጀል ፈፅመው ከሆነ፣ ወይም በመካሄድ ላይ ያለ ክስ ካለብዎት ለዜግነት ብቁ ላይሆኑ ይችላሉ።
የዜግነት ማመልከቻ ሂደት
የካናዳ ዜግነት ማመልከቻ ውስብስብ ሊመስል ይችላል። ነገር ግን ትክክለኛ ድጋፍ ካገኙ ሂደቱ ግልፅ እና ቀጥተኛ ሂደት ነው። የሚከተሉትን ጉዳዮች ማወቅ ይኖርቦታል፡-
-
የሰነድ ዝግጅት ፡ የቋሚ ነዋሪነት ካርድ፣ የቋንቋ ፈተና ውጤቶች እና የግብር ሰነዶችን ጨምሮ ሁሉም አስፈላጊ ሰነዶች እንዳሉዎት ያረጋግጡ።
-
ማመልከቻ ማስገባት ፡ የዜግነት ማመልከቻ ቅጹን ይሙሉ እና ከሰነዶችዎ እና ከማመልከቻ ክፍያዎ ጋር ያቅርቡ።
-
የሚፈጀው ጊዜ ፡ በተለምዶ በማመልከቻዎ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ብዙ ወራትን ይወስዳል።
-
የዜግነት ቃለ መጠይቅ ፡ በአንዳንድ አጋጣሚዎች ከኢሚግሬሽን ኦፊሰር ጋር የሚደረግ ቃለ መጠይቅ የሂደቱ አካል ይሆናል።
-
የዜግነት መሃላ ፡ ፈተናውን አልፈው ሁሉን መስፈርቶች ካሟሉ የዜግነት መሃላ ለመፈፀም እና የካናዳ ዜጋ ለመሆን በዜግነት ስነ ስርዓት ላይ ይገኛሉ።



