የትዳር አጋር ስፖንሰርሺፕ
የትዳር አጋር ስፖንሰርሺፕ ማለት ባለቤትዎን ወይም የትዳር አጋርዎን በቋሚነት ወደ ካናዳ ስፖንሰር ማድረግ ማለት ነው። በካናዳ የኢሚግሬሽን ህግ መ ሰረት፣ ጋብቻ በየትኛውም ሀገር በህጋዊ መንገድ የተፈፀመ ከሆነ ተቀባይነት አለው።

1
የሀገር ውስጥ ወይንስ ከሀገር ውጪ
ሁለት ዓይነት የትዳር አጋር ስፖንሰርሺፕ ፕሮግራሞች አሉ። የአገር ውስጥ የትዳር ጓደኛ ስፖንሰርሺፕ - የትዳር ጓደኛዎ በካናዳ እንደ ጊዜያዊ ነዋሪ (ጎብኚ፣ ተማሪ ወይም ሰራተኛ) ከእርስዎ ጋር የሚኖሩ ከሆነ ስፖንሰር እንዲያደርጉ ይፈቅድልዎታል። በተቃራኒው፣ የትዳር ጓደኛዎ ከካናዳ ውጭ የሚኖሩ ከሆነ፣ በውጭ አገር የትዳር አጋር ስፖንሰርሺፕ ፕሮግራም አማካኝነት ለቋሚ ነዋሪነት ስፖንሰር ማድረግ ይችላሉ። የሁለቱን ልዩነቶች ከታች ወረድ ብለው ማንበብ ይችላሉ
2
ስፖንሰር አድራጊ ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች
-
18 ዓመት እና ከዛ በላይ የሆኑ
-
የካናዳ ዜጋ ወይንም ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸው
-
ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸው ሰዎች ስፖንሰርሺፑን ለመጀመር በቋሚነት በካናዳ መኖር ያለባቸው ሲሆን የካናዳ ዜጋ ከሆኑ ደግሞ ሂደቱን ለማስጀመር በካናዳ መኖር ባይጠበቅባቸውም የትዳር አጋራቸው የካናዳ ቋሚ መኖሪያ ፈቃድ ከተሰጣቸው በኋላ በካናዳ ለመኖር እቅድ ያላቸው መሆኑን ማሳየት ይኖርባቸዋል
-
ባለፉት 5 ዓመታት ውስጥ በሌላ የትዳር አጋር አማካኝነት ስፖንሰር ያልተደረጉ
-
በፆታዊ ጥቃት እና ከባድ ወንጀል ጥፋተኛ ያልተባሉ ወይንም እስር ቤት ያልሆኑ
-
ኪሳራን ያላወጁ ወይንም ከኪሳራ ነፃ የሆኑ
-
ከካናዳ እንዲወጡ ማዘዣ ያልወጣባቸው
-
በፍርድ ቤት የታዘዙ ክፍያዎችን ለምሳሌ የልጅ ማሳደጊያ በስነስርዓት የሚከፍሉ (ከሌላ ትዳር ወይም ግንኙነት የተወለደ ልጅን ይመለከታል)
-
ምንም ዓይነት የመንግስት ዕዳ የሌለባቸው
-
ከዚህ በፊት ሌላ የትዳር አጋር ስፖንሰር አድርገው ከሆኑ ከሶስት ዓመት በላይ የሆናቸው
-
ለ 3 ዓመት የትዳር አጋርን በገንዘብ ለመደገፍ ዝግጁ የሆኑ
3
የስፖንሰርሺፕ መስፈርቱን የማያሟሉት እነማን ናቸው?
-
የትዳር አጋርን እና ልጆችን ስፖንሰር ለማድረግ የገቢ መጠንን ማሳየት እንደ መስፈርት ባይቀመጥም ስፖንሰር አድራጊው በአካል ጉዳት ምክኒያት መስራት የማይችልና የመንግስት ድጋፍ የሚያስፈልገው ካልሆነ በስተቀር በመንግስት ድጎማ ብር (የካናዳ መንግስት ለልጆች ማሳደጊያ የሚሰጠውን ገንዘብን አይጨምርም) የሚኖር እና በእሱ የሚተዳደር መሆን የለበትም፨ በመንግስት ድጎማ የሚተዳደር ከሆነ ስፖንሰር ማድረግ አይችልም፨
-
ባለፉት ሶስት ዓመታት ውስጥ የትዳር አጋርን ስፖንሰር ካደረጉ።
-
የመንግስት እዳን ወይም ከኢሚግሬሽን ጋር የተያያዙ ብድርን መክፈል ካልቻሉ።
-
ለልጅዎ ወይም የቀድሞ የትዳር አጋርዎ መወጣት የሚገባዎን ሃላፊነት በተገቢው መልኩ ካላደረጉ
-
የፆታዊ ወይንም አካላዊ ጥቃት ወንጀል ሪከርድ ካለብዎ የትዳር አጋርዎን እና ልጅዎን ስፖንሰር ለማድረግ ብቁ አይደሉም፨
በካናዳ ውስጥ ያሉ ወይንም ከካናዳ ውጪ የሚኖሩ
1
በካናዳ ውስጥ ያሉ
በካናዳ ውስጥ ለሚኖሩ የትዳር አጋር ስፖንሰርሺፕ ማመልከቻ
በዚህ ፕሮግራም መጠቀም የሚችሉት ስፖንሰር ተደራጊዎች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት የሚችሉ ናቸው::
-
በካናዳ ለመቆየት የሚያስችል ጊዜያዊ የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸው (የሌላቸውም ማመልከት የሚችሉባቸው መንገዶች አሉ)
-
የትዳር አጋራቸው የካናዳ ዜጋ የሆነ ወይንም ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ ያለው ከሆነ
-
ስፖንሰር ተደራጊዎች የስፖንሰርሺፕ ማመልከቻው ከገባ በኋላ እስከ ሚጠናቀቅ ድረስ ከካናዳ ለመውጣት እቅድ የሌላቸው
-
በዚህ ፕሮግራም የሚያመለክቱ የትዳር አጋሮች እንዲሁም እድሜያቸው ለስራ የደረሱ ልጆች ጊዜያዊ የመኖሪያ ፈቃድ ካላቸው እና ስፖንሰር ከሚያደርጋቸው የትዳር አጋር ጋር በተመሳሳይ አድራሻ እንደሚኖሩ ካሳዩ የስራ እና የትምሀርት ፈቃድን ለማግኘት ማመልክት ይችላሉ፨
-
ከላይ ያየናቸው ሌሎች የትዳር አጋር እና ልጆች ስፖንሰርሺፕ መስፈርቶች ተፈፃሚ ይሆናሉ፨
2
ከካናዳ ውጪ ለሚኖሩ የትዳር አጋር
የትዳር አጋርዎ እና ልጆችዎ ከካናዳ ውጭ የሚኖሩ ከሆነ፣ በውጭ አገር ለሚኖሩ የትዳር አጋሮች በተዘጋጀው የስፖንሰርሺፕ ፎርም አማካኝነት የቋሚ ነዋሪነት ማመልከቻውን በማስገባት ስፖንሰር ማድረግ ይችላሉ። ቁልፍ ነጥቦች የሚከተሉትን ያካትታሉ:
-
የትዳር አጋርዎ ካናዳ ውስጥ በሚኖሩበት ጊዜ በገንዘብ መርዳት አለብዎት።
-
የስፖንሰርሺፕ ማመልከቻዎ ውድቅ ከተደረገ፣ ወደ ኢሚግሬሽን ይግባኝ ክፍል (IAD) ይግባኝ የመጠየቅ መብት አልዎት። ይግባኝ መብት ያለው ከካናዳ ውጪ ያሉ የትዳር አጋርዎ እና ልጆችዎን ስፖንሰርሺፕ ማመልከቻ ብቻ ነው፨ በካናዳ ውስጥ ውስት ከእርስዎ ጋር አብረው ያሉ የትዳር አጋርዎ እና ልጅዎ ማመልከቻ ውድቅ ከተደረገ ይግባኝ የማይኖረው ሲሆን ማመልከቻውን እንደ አዲስ ማስገባት ይችላሉ፨


