top of page

በካናዳ የጥገኝነት ማመልከቻ

በአሁኑ ሰዓት ካናዳ ውስጥ ይገኛሉ? ወደ ትውልድ ሀገርዎ ቢመለሱ ለእስር፣ ለእንግልት ወይም ለሰብዓዊ መብት ጥሰት እዳረጋለሁ የሚል ከፍተኛ ፍርሃት ካለዎት፤ ለካናዳ መንግስት የጥገኝነት ጥያቄ ማቅረብ መብትዎ ነው።

ይህ ህጋዊ መብት እርስዎ እና ቤተሰብዎ ከስጋት ነጻ ሆነው አስተማማኝ እና ሰላማዊ ህይወት በካናዳ እንዲገነቡ እድል ይሰጣል።

Inland Refugee Application

በካናዳ ውስጥ ጥገኝነት ማን መጠየቅ ይችላል?

በካናዳ የጥገኝነት ጥያቄዎ ተቀባይነት ሊያገኝ የሚችለው የሚከተሉትን መሠረታዊ መስፈርቶች ሲያሟሉ ነው፦

1. በስደተኞች ኮንቬንሽን መሠረት ስደተኛ ተብለው የሚታወቁ (Convention Refugees) ከሀገራቸው ውጭ ሆነው፣ በሚከተሉት ምክንያቶች ጥቃት ወይም ስደት ይደርስብኛል የሚል ተጨባጭ ፍራቻ (Well-founded Fear of Persecution) ያላቸው ግለሰቦች፦

  • በዘር ወይም በብሔር፤

  • በሃይማኖት፤

  • በፖለቲካ አቋም፤

  • የአንድ የተወሰነ ማኅበራዊ ቡድን አባልነት (ለምሳሌ፦ ጾታን ወይም የጾታ ዝንባሌን መሠረት ያደረገ)።

2. ጥበቃ እና ከለላ የሚያስፈልጋቸው ግለሰቦች (Persons in Need of Protection) አንድ ግለሰብ ወደ ሀገሩ ቢመለስ የሚከተሉት አደጋዎች እንደሚጠብቁት በበቂ ማስረጃ ማሳየት ሲችል፦

  • በባለሥልጣናት ወይም በታጠቁ ኃይሎች የሚፈጸም ስቃይ (Danger of Torture)፤

  • ለሕይወት አስጊ የሆነ አደጋ፣ ወይም ሰብዓዊነት የጎደለው አያያዝ ወይም ቅጣት (Risk to Life or Risk of Cruel and Unusual Treatment)።

ተጨማሪ መሟላት ያለባቸው ማስረጃዎች፦ በሁለቱም መስፈርቶች የሚያመለክቱ ግለሰቦች የሚከተሉትን ነጥቦች ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል፦

  • የመንግሥት ጥበቃ ማጣት፦ የሀገሩ መንግሥት ጥበቃ ሊያደርግለት አለመቻሉን ወይም ፈቃደኛ አለመሆኑን፤

  • በሀገር ውስጥ አማራጭ ቦታ ማጣት፦ በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል በሰላም መኖር የማይቻል መሆኑን (Internal Flight Alternative)፤

  • የአደጋው ልዩነት፦ አደጋው በተለይ በአመልካቹ ላይ ያነጣጠረ መሆኑን (በሀገሪቱ ካለው አጠቃላይ የጸጥታ ችግር የተለየ)፤

  • ከሕግ ላለመሸሽ፦ የቀረበው ጥያቄ በሀገሩ በፈጸመው ወንጀል ተገቢውን ቅጣት ላለመቀበል የሚደረግ ሽሽት አለመሆኑን፤

  • የጤና ሁኔታ፦ ጥያቄው በሀገሩ ካለው ደካማ የሕክምና ሥርዓት ጋር ብቻ የተያያዘ አለመሆኑን።

2

እንዴት ማመልከት እንደሚቻል

በካናዳ የጥገኝነት ጥያቄን በሁለት መንገድ ማቅረብ ይቻላል። ሂደቱም የሚከተሉትን ዋና ዋና ደረጃዎች ያካትታል፦

  1. የጥገኝነት ጥያቄን ማሳወቅ

    • በመግቢያ ኬላ (Port of Entry)፦ ካናዳ ድንበር፣ አውሮፕላን ማረፊያ ወይም የባህር ወደብ ላይ ሲደርሱ፣ የጥገኝነት ጥያቄ ማቅረብ እንደሚፈልጉ ለድንበር ጥበቃ መኮንን (CBSA) ያሳውቁ።

    • በካናዳ ውስጥ ሆነው (Inland Claim)፦ አስቀድመው ካናዳ ውስጥ ከገቡ፣ የኢሚግሬሽን፣ ስደተኞች እና ዜግነት መሥሪያ ቤት (IRCC) ባዘጋጀው የኢንተርኔት ገጽ (Portal) አማካኝነት ጥያቄዎን ማቅረብ ይችላሉ።

  2. አስፈላጊ ሰነዶችን ማሟላት ማመልከቻው እንደ የጥገኝነት ጥያቄ መሠረት (Basis of Claim - BOC) ያሉ ወሳኝ ቅጾችን ማካተት አለበት። ይህ ቅጽ የስደተኛ ጥያቄዎ ምክንያቶችን በዝርዝር የሚገልጽ በመሆኑ፣ በውስጡ የሚሰፍሩ መረጃዎች በሙሉ ትክክለኛ፣ ዝርዝር እና ሁሉን አቀፍ መሆናቸውን ማረጋገጥ ወሳኝ ነው።

  3. የብቃት ቃለ-መጠይቅ (Eligibility Interview) ከካናዳ ድንበር አገልግሎት ኤጀንሲ (CBSA) ወይም ከኢሚግሬሽን (IRCC) መኮንን ጋር በሚደረግ ቃለ-መጠይቅ ላይ ይሳተፋሉ። በዚህ ወቅት ስለ ግል ታሪክዎ፣ ስለ ጉዞዎ እና የጥገኝነት ጥያቄ ስላቀረቡበት ምክንያት ዝርዝር መረጃ ይሰጣሉ። ጥያቄዎ ተቀባይነት ካገኘ፣ ጉዳዩ ወደ ካናዳ የኢሚግሬሽን እና ስደተኞች ቦርድ (IRB) ይተላለፋል።

  4. ለችሎት (Hearing) መዘጋጀት ጉዳይዎ ወደ ስደተኞች ቦርድ (IRB) ከተመራ በኋላ፣ በገለልተኛ ዳኛ ፊት ቀርበው ችሎት ይካሄድልዎታል። ይህ ችሎት በካናዳ ውስጥ ጥበቃ ለምን እንደሚያስፈልግዎ በዝርዝር ለማብራራት እና ማስረጃዎችዎን ለማቅረብ የሚሰጥ ወሳኝ ዕድል ነው።

የሕግ አገልግሎት እና ድጋፍ

የጥገኝነት ማመልከቻዎን እና አስፈላጊ ቅጾችን (እንደ BOC ያሉ) በጥንቃቄ ለማዘጋጀት፣ እንዲሁም በችሎት (Hearing) ወቅት እንዲወክልዎ የሕግ ባለሙያ ወይም የኢሚግሬሽን አማካሪ የመቅጠር መብት አለዎት።

 

 አቅሙ ለሌላቸው ግለሰቦች፣ እንደየግዛቱ ሁኔታ በነፃ ወይም በዝቅተኛ ክፍያ የሕግ ድጋፍ የሚሰጥበት አሠራር (Legal Aid) ሊመቻች ይችላል።

3

ሒደቱ ምን ይመስላል

የጥገኝነት ማመልከቻዎን ለኢሚግሬሽን መሥሪያ ቤት (IRCC) ካስገቡ በኋላ፣ የሚከተሉትን መሠረታዊ አገልግሎቶች የማግኘት መብት ይኖርዎታል፦

​​

  1. የሥራ ፈቃድ፦ የጥገኝነት ማመልከቻዎ በሂደት ላይ እያለ፣ በካናዳ ውስጥ በሕጋዊ መንገድ ለመሥራት የሚያስችል ክፍት የሥራ ፈቃድ (Open Work Permit) ማመልከት እና ማግኘት ይችላሉ።

  2. የጤና ጥቅማጥቅሞች (IFHP)፦ በፌዴራል መንግሥት የሚደገፈው የጊዜያዊ የጤና ፕሮግራም (Interim Federal Health Program) ተጠቃሚ ይሆናሉ። ይህም ለድንገተኛ ሕክምና፣ ለሐኪም ምርመራ እና ለሌሎች መሠረታዊ የጤና አገልግሎቶች ሽፋን ይሰጣል።

4

ጥገኝነት ማቅረብ የማይችሉት

የጥገኝነት ማመልከቻዎን ከማስገባትዎ በፊት፣ ከታች በተዘረዘሩት ምክንያቶች ማመልከቻዎ ውድቅ ሊደረግ እንደሚችል ማወቅ ጠቃሚ ነው፦

  • ከዚህ በፊት ጥያቄ አቅርበው ከሆነ፡ ከዚህ ቀደም ለካናዳ መንግስት የጥገኝነት ጥያቄ አቅርበው ውድቅ ከተደረገብዎ፣ ሂደቱን አቋርጠው ከሆነ ወይም ጥያቄውን ሰርዘው ከሆነ።

  • በሌላ ሀገር ጥበቃ ካገኙ፡ በሌላ ሀገር (ከካናዳ ውጪ) የጥገኝነት ጥያቄዎ ተቀባይነት አግኝቶ ጥበቃ የሚደረግልዎት ከሆነ።

  • የወንጀል ወይም የደህንነት ስጋት፡ በከባድ ወንጀል ወይም በሰብዓዊ መብት ጥሰት የተሳተፉ ከሆነ፣ እንዲሁም ለካናዳ ህዝብ ደህንነት ስጋት ናቸው ተብሎ ከታመነ።

  • ከአሜሪካ ወደ ካናዳ የገቡ ከሆነ (Safe Third Country Agreement)፡ በካናዳ እና በአሜሪካ መካከል ባለው ስምምነት መሰረት፣ አሜሪካን አቋርጠው ወደ ካናዳ የገቡ ከሆነ ጥያቄዎ ተቀባይነት ላይኖረው ይችላል። ( ለዚህ ህግ አንዳንድ ልዩ ሁኔታዎች ወይም Exceptions ስላሉ ያማክሩን።)

!
Widget Didn’t Load
Check your internet and refresh this page.
If that doesn’t work, contact us.
Refugee-web-banner.png.webp

ያግኙን

+1 647-563-6059

  • Facebook
  • LinkedIn

Thanks for submitting!

bottom of page