
የቤተሰብ ስፖንሰርሺፕ
የካናዳ መንግስት የትዳር አጋርን፣ ልጆችን፥ ወላጆችን እና አያቶችን እንዲሁም ሌሎች የቤተሰብ አባላትን በቋሚ ነዋሪነት ወደካናዳ ስፖንሰር አድርገው እንዲያመጡ ይፈቅድልዎታል።
የትዳር አጋር ስፖንሰርሺፕ
.png)
የትዳር አጋርዎን ወይንም አብረው ከአንድ ዓመት በላይ የኖሩትን እጮኛዎን እና ልጆችዎን በቋሚ ነዋሪነት ወደካናዳ ማምጣት የሚችሉበት ፕሮግራም ነው።
የትዳር አጋርዎ አብረዎት ካናዳ ውስጥ የሚኖሩ ከሆነ በሀገር ውስጥ የትዳር አጋር ስፖንሰርሺፕ ፕሮግራም አማካኝነት ስፖንሰር ማድረግ የሚችሉ ሲሆን የትዳር አጋርዎ ከካናዳ ውጪ ከሆኑ ከካናዳ ውጪ ላሉ የትዳር አጋሮች በተዘጋጀው የስፖንሰርሺፕ ፕሮግራም አማካኝነት የትዳር አጋርዎን እና ልጆችዎን ማምጣት ይችላሉ።
የልጆች ስፖንሰርሺፕ

በካናዳ የኢሚግሬሽን ሕግ መሠረት፣ በቤተሰብ ስፖንሰርሺፕ ፕሮግራም አማካኝነት ልጆችን በቋሚነት ወደ ካናዳ ማምጣት የሚቻለው ዕድሜያቸው ከ22 ዓመት በታች ለሆኑና ትዳር ላልመሠረቱ (ያላገቡ) ልጆች ብቻ ነው።
ሆኖም ዕድሜያቸው 22 ዓመትና ከዚያ በላይ ቢሆንም፣ በአእምሮአዊ ወይም በአካላዊ ውስንነት ምክንያት በራሳቸው መተዳደር የማይችሉና በወላጆቻቸው ላይ ጥገኛ የሆኑ ልጆች ስፖንሰር ሊደረጉ ይችላሉ። ከእነዚህ ልዩ ሁኔታዎች ውጭ፣ ዕድሜያቸው 22 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆኑ ልጆችን በቤተሰብ ስፖንሰርሺፕ ፕሮግራም ወደ ካናዳ ማምጣት አይቻልም።


.png)