top of page

የጉብኝት ቪዛ

Visit
!
Widget Didn’t Load
Check your internet and refresh this page.
If that doesn’t work, contact us.

የጉብኝት ቪዛ ለማግኘት ምን ምን ማሟላት ያስፈልጋል?

በካናዳ የቪዛ አሰጣጥ ሥርዓት ውስጥ እንደ ዜግነት ሁኔታ ሁለት ዓይነት የቪዛ ዓይነቶች አሉ። እንደ ኢትዮጵያ ካሉ የቪዛ ግዴታ ካለባቸው የአፍሪካ ሀገራት ለሚመጡ ዜጎች፣ በፓስፖርት ላይ የሚለጠፍ የጎብኝ ቪዛ (TRV) የሚሰጥ ሲሆን፤ ከአውሮፓ እና ከሌሎች የቪዛ ነፃ መብት ካላቸው ሀገራት ለሚመጡ ዜጎች ደግሞ በኤሌክትሮኒክ መንገድ ከፓስፖርት ጋር የሚገናኝ ኢ-ቲኤ (eTA) ይሰጣቸዋል። የሁለቱ ዋና ልዩነት ኢ-ቲኤ (eTA) በአጭር ጊዜ (ብዙውን ጊዜ በ24 ሰዓት ውስጥ) የሚሰጥ ሲሆን፣ በፓስፖርት ላይ የሚለጠፈው ቪዛ ግን እንደየሀገሩ ሁኔታ ከ30 እስከ 90 ቀናት ወይም ከዚያ በላይ ሊፈጅ ይችላል። በተጨማሪም በፓስፖርት ላይ የሚለጠፈው ቪዛ እንደ አመልካቹ ፍላጎትና እንደ ውሳኔው ለአንድ ጊዜ (Single Entry) ወይም ለተደጋጋሚ ጊዜ (Multiple Entry) ሊሰጥ የሚችል ሲሆን፤ ኢ-ቲኤ (eTA) ግን በቋሚነት እስከ 5 ዓመት ድረስ ለተደጋጋሚ ጉዞ የሚያገለግልና በአንድ ጊዜ መግቢያ እስከ 6 ወር ለመቆየት የሚያስችል ነው።

2

የጉብኝት ቪዛ ለማግኘት ምን ምን ማሟላት ያስፈልጋል?

የጎብኝ ቪዛ ለማግኘት ከመማልከታችን በፊት፣ ወደ ካናዳ የምንሄድበትን ምክንያት በግልጽ ማዘጋጀት ዋነኛው ተግባር ነው። በጎብኝ ቪዛ ወደ ካናዳ ከሚመጣባቸው ዋና ዋና ምክንያቶች መካከል፦

  • ካናዳን እንደ ማንኛውም ጎብኚ (ቱሪስት) ለመጎብኘት፤

  • በካናዳ የሚኖር ቤተሰብን ለመጠየቅ ወይም በማኅበራዊ ዝግጅቶች (ሰርግ፣ ክርስትና፣ ምርቃት እና ቀብር) ላይ ለመገኘት፤

  • በሥራ ስብሰባዎች፣ ኮንፈረንሶች እና ሥልጠናዎች ላይ ለመሳተፍ፤

  • በስፖርታዊ ውድድሮች ላይ ለመሳተፍ።

ከመጀመሪያው ምክንያት (ለቱሪዝም) ውጭ ያሉት ምክንያቶች በሙሉ ከካናዳ የሚላክ የጥሪ ደብዳቤ (Invitation Letter) ማቅረብን ይጠይቃሉ።

የጥሪ ደብዳቤ አስፈላጊ ቢሆንም፣ ከዛ በላይ ግን አመልካቾች ጉብኝታቸውን አጠናቅቀው ወደ ሀገራቸው ለመመለሳቸው ዋስትና የሚሆኑ ማስረጃዎችን ማቅረብ ይኖርባቸዋል። እነዚህ ማስረጃዎች አመልካቹ ከሀገሩ ጋር ያለውን ጠንካራ ቁርኝት (Home Ties) የሚያሳዩ መሆን አለባቸው። ለምሳሌ፦

  • የቤተሰብ ኃላፊነት፦ትዳር እና የልጆች ወላጅ መሆን፤  ጡረተኛ ወላጆችን ወይም በኃላፊነት የሚደገፉ የቤተሰብ አባላትን መርዳት፤

  • የሥራ ሁኔታ፦ ጥሩ ገቢ የሚያስገኝ ቋሚ የሥራ ቅጥር መኖር፤

  • ማኅበራዊ ትስስር/ተጽዕኖ ፈጣሪነት፦ በሀገር ውስጥ ያለ ሙያዊ ታዋቂነት ወይም ማኅበራዊ ተጽዕኖ

  • ኢኮኖሚያዊ ቁርኝት፦ የንግድ ድርጅት፣ ንብረት ወይም ሀብት መኖር

ተጨማሪ መመሪያዎች

  • ፓስፖርት፦ አመልካቾች ቪዛ ለማመልከት ቢያንስ የ6 ወር ቀሪ  ጊዜ ያለው ፓስፖርት መያዝ ይኖርባቸዋል።

  • የመግቢያ ፈቃድ ውሳኔ፦ ከኤምባሲ ቪዛ ማግኘት ማለት ወደ ካናዳ ለመግባት በሩን እንደ ማንኳኳት ነው። ወደ ካናዳ እንዲገቡ የመጨረሻውን ውሳኔ የሚሰጠው በኤርፖርት የሚገኘው የድንበር ጥበቃ መኮንን (Border Services Officer) በመሆኑ፣ በኤርፖርት ለሚጠየቁ ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ መሆን ያስፈልጋል።

ያግኙን

+1 647-563-6059

  • Facebook
  • LinkedIn

እናመሰግናለን!

bottom of page