
የጉብኝት፥ትምህርትና የስራ ቪዛ
ጊዜያዊ ነዋሪነት፣ የውጭ ሀገር ዜጎች ለተወሰነ ጊዜ እና ለተለየ ዓላማ በካናዳ ውስጥ እንዲቆዩ የሚፈቅድ የሕግ ሁኔታ ነው። ይህም ግለሰቦች ላልተወሰነ ጊዜ እንዲኖሩ ከሚፈቅደው የቋሚ ነዋሪነት (Permanent Residency) ሁኔታ የተለየ ነው። ጊዜያዊ ነዋሪዎች ወደ ካናዳ የሚመጡት እንደ ቱሪዝም፣ ሥራ ወይም ትምህርት ላሉ የተለዩ ዓላማዎች ነው።
ጊዜያዊ ነዋሪነት እንደ ቋሚ ነዋሪ ወይም እንደ ካናዳ ዜጋ ተመሳሳይ መብቶችንና ጥቅማጥቅሞችን የማያስገኝ ሲሆን፣ ግለሰቡም በካናዳ የኢሚግሬሽን ባለሥልጣናት (IRCC) በተቀመጡት ደንቦችና ቅድመ ሁኔታዎች የመገዛት ግዴታ አለበት።
አንድ የውጭ ሀገር ዜጋ በጊዜያዊ ነዋሪነት ወደ ካናዳ ሊገባባቸው የሚችልባቸው በርካታ ምድቦች አሉ። በብዛት የሚታወቁት የጊዜያዊ ነዋሪነት ዓይነቶች የሚከተሉት ናቸው፦
የጉብኝት ቪዛ
.png)
የውጭ ሀገር ዜጎች ወደ ካናዳ ለመግባት እንደ ዜግነታቸው ከሚከተሉት ሁለት ሰነዶች አንዱ ያስፈልጋቸዋል፦
1. የጎብኝ ቪዛ (Visitor Visa / TRV)፦ የቪዛ ግዴታ ካለባቸው ሀገራት የሚመጡ ዜጎች ወደ ካናዳ ለመግባት የሚያስፈልጋቸው ይፋዊ የጉዞ ሰነድ ነው። ይህ ቪዛ በፓስፖርትዎ ላይ የሚለጠፍ ሲሆን፣ በአብዛኛው እስከ 6 ወር ድረስ በካናዳ ውስጥ እንዲቆዩ ይፈቅዳል።
2. የኤሌክትሮኒክ የጉዞ ፈቃድ (Electronic Travel Authorization - eTA)፦ የቪዛ ነፃ መብት ካላቸው ሀገራት የሚመጡ ዜጎች በሕግ የተቀመጠላቸው የጉዞ ፈቃድ ነው። ኢ-ቲኤ (eTA) በፓስፖርትዎ ላይ የማይለጠፍ ነገር ግን በኤሌክትሮኒክ መንገድ ከፓስፖርትዎ ጋር የተያያዘ ፈቃድ ነው። በአየር መንገድ ወደ ካናዳ ለመግባት የግድ የሚያስፈልግ ሲሆን፣ እስከ 5 ዓመታት ወይም ፓስፖርትዎ እስኪያልቅ ድረስ ያገለግላል።
ሱፐር ቪዛ

ሱፐር ቪዛ፣ የካናዳ ዜጋ ወይም ቋሚ ነዋሪ የሆኑ ግለሰቦች ወላጆቻቸውንና አያቶቻቸውን ለረጅም ጊዜ ጉብኝት ወደ ካናዳ እንዲጋብዙ የተነደፈ ልዩ የቪዛ ዓይነት ነው። ይህ ቪዛ ከመደበኛው የጎብኝ ቪዛ (በአንድ ጊዜ እስከ 6 ወር ብቻ ከሚፈቅደው) በተለየ መልኩ፣ ባለይዞታው በካናዳ ውስጥ በአንድ ጊዜ እስከ 5 ዓመታት ድረስ እንዲቆይ ይፈቅዳል።
ቪዛው እንደ ፓስፖርቱ ተቀባይነት ጊዜ እስከ 10 ዓመታት ሊያገለግል የሚችል ሲሆን፣ በነዚህ ዓመታት ውስጥ ደጋግሞ ወደ ካናዳ ለመመላለስ (Multiple Entry) ያስችላል።

.png)
.png)
