የልጆች ስፖንሰርሺፕ
የካናዳ ቤተሰብ ስፖንሰርሺፕ ፕሮግራም የካናዳ ዜጎች እና ቋሚ ነዋሪዎች ልጆቻቸው በቋሚነት በካናዳ እንዲኖሩ የመኖሪያ ፈቃድ እንዲያገኙ እድልን ያመቻቻል። ይህ ፕሮግራም በተፈጥሮ የተወለዱ እና የማደጎ ልጆችን የሚመለከት ሲሆን ይህም ቤተሰቦች በካናዳ ውስጥ አብረው እንዲኖሩ እድል ይሰጣል።
ልጅዎን በተሳካ ሁኔታ ስፖንሰር ለማድረግ፣ በካናዳ የኢሚግሬሽን፣ ስደተኞች እና ዜግነት (IRCC) የተቀመጠውን የብቃት መስፈርት ማሟላት ይኖርቦታል።
1
ስፖንሰር ማድረግ የሚችሉት የትኞቹን ልጆችዎን ነው?
ልጆች (የጋራ ልጆችን፥ ከቀድሞ ትዳር የተወለዱ የእርስዎ ሆነ የባለቤትዎ ልጆች እና በማደጎ የምታሳድጉትን ይጨምራል) የሚከተሉትን መስፈርቶች ካሟሉ ስፖንሰር መደረግ ይችላሉ፡
-
ከ22 ዓመት በታች የሆኑ እና
-
ባል ወይንም ሚስት የሌላቸው (ያላገቡ)
የልጅ ልጅዎ ከ 22 ዓመት በታች ከሆነ ስፖንሰር ማድረግ የሚችሉ ሲሆን ይህን ለማድረግ ግን የገንዘብ አቅሙ እንዳልዎት ማሳየት ይጠበቅቦታል፨
ከ22 ዓመት በላይ የሆኑ ልጆችዎ ወይንም የልጅ ልጅዎ ከዚህ በታች ያሉትን ሁለት መስፈርቶች ካሟሉ ስፖንሰር መደረግ ይችላሉ፨
-
በአዕምሯዊ ወይም አካላዊ የእድገት ውስንነት ወይንም ጉዳት ምክኒያት ራሳቸውን መደገፍ የማይችሉ እና
-
በዚህም ምክኒያት 22 ዓመት ከመሆናቸው አስቀድሞ በቤተሰባቸው ላይ ጥገኛ የሆኑ
2
ልጆችዎን ስፖንሰር ለማድረግ የሚያስፈልጉ መስፈርቶች
ልጆቻችሁን ስፖንሰር ለማድረግ የሚከተሉትን መመዘኛዎች ማሟላት አለቦት።
-
የካናዳ ዜጋ ወይም ቋሚ ነዋሪ መሆን።
-
18 ዓመት ወይም ከዚያ በላይ ።
-
በእስር ቤት ያልሆኑ፣ በከባድ ወንጀሎች ያልተከሰሱ እና በዕዳ ያልተዘፈቁ መሆን ይኖርቦታል።
የግንኙነት ማረጋገጫ
በእርስዎ እና በ ልጅዎ መካከል ያለውን ግንኙነት የሚያረጋግጡ ሰነዶችን ማቅረብ አለብዎት፣ ለምሳሌ፡-
-
የልደት የምስክር ወረቀት.
-
የማደጎ ወረቀቶች.
3
ስፖንሰር ለሚያደርጓቸው ልጆችዎ የሚኖርብዎት የገንዘብ ሀላፊነቶች
ልጅን ስፖንሰር ለማድረግ የገንዘብ አቅምዎን ማሳየት ወይንም የተለየ የገቢ መስፈርቶችን ማሟላት አይጠበቅብዎትም፨ ነገር ግን በመንግስት ድጎማ የማይኖሩ መሆኑን እና ልጆችዎን በተገቢ መልኩ በገንዘብ መደገፍ እንደሚችሉ ማሳየት ይኖርቦታል።
ነገር ግን፣ ልጅዎ ልጅ ካለው (የእርስዎ የልጅ ልጅ)፣ መላውን የቤተሰብ አባል ለመደገፍ የሚያስችል በቂ ገቢ እንዳለዎት ማሳየት ይኖርቦታል።
የገንዘብ ድጋፍ የሚቆይበት ጊዜ ፡ የገንዘብ ድጋፍ መስጠት የሚኖርብዎት የጊዜ ርዝማኔ በልጁ ዕድሜ ላይ የተመሰረተ ነው፡-
-
ከ16 አመት በታች ከሆነ፡ ለ10 ዓመት ወይም ልጁ 22 አመት እስኪሞላው ድረስ (ረዘም ያለ ጊዜ የሚወስደው ተፈጻሚ ይሆናል)።
-
16 አመት ወይም ከዚያ በላይ ፡ ለ 3 ዓመት የገንዘብ ድጋፍ መስጠት አለቦት ወይም ልጁ 25 ዓመት እስኪሞላው ድረስ (ረዘም ያለ ጊዜ የሚወስደው ተፈጻሚ ይሆናል)።



