1
የስፖንሰርሺፕ አማራጮች
ስደተኞች በግል ስፖንሰርሺፕ (Private Sponsorship) ወደ ካናዳ መምጣት የሚችሉባቸው ሶስት ህጋዊ መንገዶች አሉ።
1. የቡድን አምስት ስፖንሰርሺፕ (Group of Five)
-
ይህ አምስት የካናዳ ዜግነት ወይም የቋሚ ነዋሪነት (Permanent Resident) ፈቃድ ያላቸው ግለሰቦች በመሰባሰብ ስደተኛን ስፖንሰር የሚያደርጉበት መንገድ ነው።
-
ቅድመ ሁኔታ: ስደተኛው ከ UNHCR ወይም ካለበት ሀገር መንግስት የተሰጠ የስደተኛነት ማረጋገጫ ወረቀትሊኖረው ይገባል።
2. የማህበረሰብ ስፖንሰርሺፕ (Community Sponsors)
-
ስደተኞችን ስፖንሰር ለማድረግ የተቋቋሙ የማህበረሰብ ድርጅቶች ወይም ማህበራት የሚያመጡበት መንገድ ነው።
-
ቅድመ ሁኔታ: ልክ እንደ ቡድን አምስት ሁሉ፣ ስደተኛው የስደተኛነት ማረጋገጫ ወረቀት (Refugee Status Recognition) ሊኖረው ግድ ነው።
3. ስምምነት ያላቸው ተቋማት (Sponsorship Agreement Holders - SAHs)
-
ከካናዳ ኢሚግሬሽን ጋር ስደተኞችን ለማምጣት ውል የተፈራረሙ ተቋማት (አብዛኛውን ጊዜ የሃይማኖት ተቋማት ወይም ግብረ-ሰናይ ድርጅቶች) ናቸው።
-
ልዩ ጥቅም: በዚህ መንገድ ስፖንሰር የሚደረጉ ስደተኞች የስደተኛነት ማረጋገጫ ወረቀት (Refugee Status Document) ባይኖራቸውም ስፖንሰር ሊደረጉ ይችላሉ።
⚠️ ማሳሰቢያ
የካናዳ መንግስት ማመልከቻዎችን ለማስተካከል በወሰደው እርምጃ መሰረት፣ "የቡድን አምስት (Group of 5)" እና "የማህበረሰብ ስፖንሰርሺፕ (Community Sponsors)" ፕሮግራሞች እስከ ታህሳስ 2025 (December 2025) ድረስ፦ ለጊዜው ታግደዋል (Paused)።
በአሁኑ ሰዓት ክፍት ሆኖ እያገለገለ የሚገኘው በስምምነት ስፖንሰር የሚያደርጉ ተቋማት (SAHs) አማራጭ ብቻ ነው።
2
መስፈርቶች
ስደተኞችን ወደ ካናዳ ስፖንሰር አድርጎ ለማምጣት፣ ስፖንሰሮችም ሆኑ ስደተኞች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
1. ለስፖንሰሮች (Sponsors)
ስፖንሰር የሚያደርጉ ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች የሚከተሉትን ማሟላት አለባቸው፦
-
ህጋዊ ሁኔታ፡ የካናዳ ዜጋ (Citizen) ወይም ቋሚ ነዋሪ (Permanent Resident) መሆን።
-
የገንዘብ አቅም፡ ስደተኞችን ለአንድ ዓመት ለመደገፍ የሚያስችል በቂ የገንዘብ እና የመቋቋሚያ በጀት እንዳላቸው ማረጋገጥ።
-
የሰፈራ እቅድ (Settlement Plan): ስደተኞቹ ካናዳ ከገቡ በኋላ እንዴት እንደሚቋቋሙ የሚያሳይ ግልጽ እና ተግባራዊ እቅድ ማቅረብ (ለሁሉም ስፖንሰርሺፕ ዓይነቶች ግዴታ ነው)።
2. ለስደተኞች (Refugees)
በካናዳ ኢሚግሬሽን ህግ መሰረት፣ ስፖንሰር የሚደረጉ ሰዎች ከሚከተሉት ሁለት የስደተኛ አይነቶች በአንዱ ሊመደቡ ይገባል፦
ሀ. የኮንቬንሽን ስደተኞች (Convention Refugees Abroad Class) እነዚህ ስደተኞች ሀገራቸውን ጥለው የወጡት በሚከተሉት ምክንያቶች ለህይወታቸው ወይም ለደህንነታቸው ስጋት ስላለባቸው ነው፦
-
በዘር (Race)
-
በሃይማኖት (Religion)
-
በብሔር/ዜግነት (Nationality)
-
በፖለቲካ አቋም (Political Opinion)
-
በአንድ የተወሰነ ማህበራዊ ቡድን አባልነት (Membership in a particular social group)
ለ. በስደተኛ-መሰል ሁኔታ ላይ ያሉ (Country of Asylum Class) ይህ ምድብ የሚያካትተው በግል ከሚደርስባቸው ጥቃት ይልቅ፣ በአገራቸው ባለው አጠቃላይ ሁኔታ ምክንያት የተሰደዱትን ነው፦
-
በጦርነት ወይም በትጥቅ ግጭት ምክንያት የተሰደዱ።
-
በመጠነ ሰፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እና ሁከት ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው።
⚠️ ወሳኝ ቅድመ ሁኔታ፡ "ዘላቂ መፍትሄ" (Durable Solution)
ስደተኛው ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ቢያሟላም፣ ስፖንሰር ለመደረግ የሚከተሉትን ተጨማሪ ነጥቦች ማረጋገጥ አለበት፦
-
ከሀገር ውጪ መሆን፡ ስደተኛው ከትውልድ ሀገሩ ወይም ከመኖሪያ ሀገሩ ውጪ መሆን አለበት።
-
ዘላቂ መፍትሄ ያጣ (No Durable Solution)፡ ስደተኛው አሁን ባለበት ሁኔታ ሌላ አማራጭ የሌለው መሆን አለበት። ይኸውም፦
-
ወደ ትውልድ ሀገሩ በሰላም መመለስ የማይችል።
-
አሁን ባለበት የስደት ሀገር (Host Country) ዜግነት አግኝቶ ወይም ተረጋግቶ መኖር የማይችል።
-
ወደ ሌላ ሶስተኛ ሀገር ሄዶ የመኖር እድል የሌለው።
-
3
የስፖንሰርሺፕ ውድቅ የሚያስደርጉ የተለመዱ ምክንያቶች
የስደተኞች ስፖንሰርሺፕ ማመልከቻ በኢሚግሬሽን ቢሮ ተቀባይነት እንዳያገኝ (Refused) የሚያደርጉ የተለመዱ ስህተቶች የሚከተሉት ናቸው፦
1. የገንዘብ አቅም ማነስ (Financial Requirement)
-
ስፖንሰሮቹ በካናዳ መንግስት የተቀመጠውን ዝቅተኛ የገቢ መጠን (Minimum Necessary Income) ማሟላት ካልቻሉ።
-
ወይም ለስደተኛው የሚያስፈልገውን የተቀማጭ ገንዘብ መጠን ማስያዝ ካልቻሉ።
2. የሰነድ ስህተቶች (Forms and Documentation)
-
ጊዜያቸው ያለፈባቸው (Outdated) ፎርሞች፡ የኢሚግሬሽን ቢሮ በየጊዜው ፎርሞችን ስለሚቀያይር፣ የድሮውን ቨርዥን መጠቀም።
-
ያልተሟላ መረጃ፡ ፎርሞችን በትክክል አለመሙላት ወይም መፈረም ያለበትን ቦታ አለመፈረም።
3. የቤተሰብ አባልነት መስፈርት (Family Eligibility)
-
አብረው እንዲመጡ የተጠየቁት የቤተሰብ አባላት በካናዳ ህግ መሰረት "የቤተሰብ አባል" (Declaring ineligible family members) ተብለው የማይቆጠሩ ከሆነ። (ለምሳሌ፡ እድሜው ያለፈበት ልጅ ወይም ያገባ ልጅን እንደ ጥገኛ ማቅረብ)።
4. ወደ ሀገር መግባት የሚከለክሉ ሁኔታዎች (Inadmissibility) ስደተኛው በሚከተሉት ምክንያቶች ወደ ካናዳ እንዳይገባ ህጉ የሚከለክለው ከሆነ፡
-
ወንጀል (Criminality): በከባድ ወንጀል የተሳተፈ ከሆነ።
-
ደህንነት (Security): ለካናዳ ደህንነት ስጋት ነው ተብሎ ከታመነ።
-
ጤና (Medical): በካናዳ ህዝብ ላይ የጤና ስጋት የሚፈጥር ወይም በካናዳ የጤና ስርዓት ላይ ከፍተኛ ጫና (Excessive demand) የሚፈጥር የጤና እክል ካለበት።
የስደተኞች ስፖንሰርሺፕ
የስደተኞች ስፖንሰርሺፕ ከችግር ሸሽተው በሰው ሀገር ላይ ያሉ ስደተኞችን ደህንነተቻው እና ክብራቸው ተጠብቆ ህይወታቸውን እንደገና እንዲገነቡ የሚያስችል መንገድ ነው።
እርስዎም እንደ ግለሰብ ወይንም በድርጅትዎ አማካኝነት ስደተኛን ስፖንሰር የማድረግ ፍላጎት ካሎት፣ ኤምቲኤ የኢሚግሬሽን አገልግሎት የስፖንሰርሺፕ ማመልከቻዎ የተሳካ እንዲሆንልዎ አስተማማኝ ሙያዊ አገልግሎት ልንሰጥዎ ዝግጁ ነን።




